Training

Law of Family

የስልጠናው ርዕስ፡          የኢትዮጲያ የቤተሰብ ሕግ

የስልጠናው ዓላማ፡          ከዚህ ስልጠና በኋላ ተሳታፊዎች

  • ጋብቻ የሚፈፀምባቸውን ስርዓቶች መተንተን፣
  • ጋብቻ ለመፈፀም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች መዘርዘርና ተግባራዊነታቸውን መገምገም፣
  • ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነትና በንብረት በኩል ስለሚኖረው ውጤት ማብራሪያ መስጠት፣
  • ጋብቻ የሚፈርስባቸውን ምክንያቶች መዘርዘር፣
  • በፍቺ በኩል የተደረጉትን መሻሻሎች መተንተንና መገምገም፣
  • አዲሱ የቤተሰብ ሕግ በሴቶች መብቶች አኳያ ያደረጋቸውን መሻሻሎች ማብራራት፣
  • አባትነት የሚረጋገጥባቸውን መንገዶች መግለፅ፣
  • የጉዲፈቻስምምነትማድረግየሚቻልበትንሁኔታዎችማስረዳት፣
  • ቀለብ የመስጠት ግዴታዎች አፈፃፀሞችን መግለፅና ማብራራት፣
  • ለአንዳንድ ቤተሰብ ነክ ጉዳዮች ውሳኔ መስጠት ይችላሉ፡፡

የስልጠናው ይዘት፡           ጋብቻ መፈፀምና ቤተሰብ መመስረት፣የጋብቻ ውጤት፣የጋብቻ መፍረስ፣የጋብቻ ማስረጃ እና ጋብቻ ሳይፈፀም እንደ ባልና ሚስት አብሮ ስለመኖር፣ስለመውለድ፣ጉዲፈቻ እንዲሁም  ቀለብ የመስጠት ግዴታ ናቸው፡፡

ለስልጠናው የተመደበው ጊዜ፡    5 ቀናት

የስልጠናው ተሳታፊዎች፡       በፌደራልና በክልል የሲቪል ሰርቪስ መስሪያቤቶች የሚገኙ የከፍተኛ፣መካከለኛ እና ዝቅተኛ ደረጃ አመራሮችና ፕሮፌሽናሎች እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ናቸው፡፡

የስልጠናው ዘዴ፡           የስልጠናዉ አሰጣጥ የአሰልጣኞች እና ሰልጣኞችን መማማር እና የጋራ ተሳትፎ መሰረት ያደረገ ሲሆን በቡድን ስራ፣በመልመጃ፣እና ከድርጅቱ እና ከሰልጠኞች የግል ተሞክሮ ጋር የተያያዙ ተዛማጅ ጥናቶችን በማድረግ የሚከወንነዉ፡፡ በእያንዳንዱ የስልጠና መንገድ ስልጠናዉን ከአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጲያ የቤተሰብ ሕግ ተግዳሮቶች ጋር ለማገናኘት ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡

Newsletter

Don't want to miss our interesting news and updates! Make sure to join our newsletter list.

Contact us

Please do not hesitate to contact us:

  • MO to TH: 8:15 - 12:15 / 1:30 pm - 5:15 pm
  • FR: 8:15 - 11:30 / 1:30 pm - 5:15 pm
  • Hot line: +251-116-46-30-15
  • Student Registrar: +251-118-33-31-93 / 94
  • International and Public Relations Directorate:

  • Phone: +251-116-46-28-87

PoBox: 5648

Connect with us

We're on Social Networks. Follow us & get in touch.