Employment and Labor Law
የስልጠናው ርዕስ፡ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ
የስልጠናው ዓላማ: ከዚህ ስልጠና በኋላ ተሳታፊዎች
- የአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረታዊ ሃሳቦችን ለመረዳት ይችላሉ፣
- በአሰሪና ሰራተኛ መካከልበቅጥር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በምን መልኩ እንደሚፈፀም ይረዳሉ፣
- የስራ ውል አመሰራረትና የቆይታ ጊዜው ምን ያህል እንደሆነ ያስረዳሉ፣
- የአሰሪና የሰራተኛ ግዴታዎችን በዝርዝር ያስቀምጣሉ፣
- የህብረት ግንኙነት የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ይረዳሉ እንዲሁም
- በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚነሱ የስራ ክርክሮች እንዴት እንደሚዳኙ ይገነዘባሉ፡፡
የስልጠናውይዘት፡ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረቱና ዓላማው፣የአዋጅ ቁጥር 337/36 የተፈፃሚነት ወሰን፣የሥራ ውል፣ የአሰሪና የሰራተኛ ግዴታዎች፣የህብረት ግንኙነት እንዲሁም የሥራ ክርክር ናቸው፡፡
ለስልጠናው የተመደበው ጊዜ፡ 5 ቀናት
የስልጠናው ተሳታፊዎች፡ በፌደራልና በክልል የሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የከፍተኛ፣መካከለኛ እና ዝቅተኛ ደረጃ አመራሮችና ፕሮፌሽናሎች እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ናቸው፡፡
የስልጠናው ዘዴ፡ የስልጠናዉ አሰጣጥ የአሰልጣኞች እና ሰልጣኞችን መማማር እና የጋራ ተሳትፎ መሰረት ያደረገ ሲሆን በቡድን ስራ፣በመልመጃ፣እና ከድርጅቱ እና ከሰልጠኞች የግል ተሞክሮ ጋር የተያያዙ ተዛማጅ ጥናቶችን በማድረግ የሚከወንነዉ፡፡ በእያንዳንዱ የስልጠና መንገድ ስልጠናዉን ከአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ ተግዳሮቶች ጋር ለማገናኘት ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡