የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 15ኛዉን የብሔር ብሄረሰቦችናሕዝቦች ቀን “እኩልነትና ሕብረ-ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቀል ከ23/3/2013-24/3/2013 ዓ.ም በአባይ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ፡፡
በመክፈቻ ንግግራቸዉ ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር የተዋቀረችዉ በብሄር ብሔረሰቦችናህዝቦች ስብስብ ነዉ ፡፡ በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መንግስታት ተለዋዉጠዋል፤ የተለያዩ ችግሮችም አልፈናል ነገር ግን ኢትዮጲያ አንድነቷንናሉአላዊነቷን ጠብቃ ቆየታለች ወደፊትም ትቀጥላለች፡፡ብዝኃነታችንን ደግሞ ለሰላም፣ለልማትና ለሁለንተናዊ ብልፅግና ይበልጥ መጠቀም ይገባናል ብለዋል፡፡እኛ ኢትዮጵያዉያን የቆየውን የአብሮነትና የአንድነት እሴቶች ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን የለዉጥ ጉዞ ወደ ፊት ማራመድ ከሁሉም ሀገር ወዳድ የሚጠበቅ ነዉ ብለዋል፡፡