የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በወሊሶ ካምፓስ ያስገነባዉን ደረጃውን የጠበቀ ለመዋዕለ ሕጻናት አገልግሎት የሚውል ህንጻ ለከተማ አስተዳደሩ ርክክብ ሊያደርግ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በወሊሶ ከተማ በማስገንባት ላይ ካለው የወሊሶ ካምፓስ ግንባታ ጎን ለጎን በልዩ ትኩረት በማከናወን ላይ ባለው የማህበረሰብ አገልግሎት መሰረት ለአካባቢው ማህበረሰብ ልጆች የትምህርት አገልግሎት የሚውል የመዋዕለ ህጻናት ህንጻም ሲያስገነባ ቆይቷል፡፡ የዩንቨርስቲው የሥራ አመራር ቦርድም የመዋዕለ ህጻናቱን የግንባታ ሂደት ከጅምሩ ጀምሮ በልዩ ሁኔታ እና በአካል ቦታው ላይ በመገኘት ጭምር ሲከታተለው የቆየ ሲሆን በተደረገው ክትትልም የግንባታ ሂደቱ በታቀደው ሁኔታ ተጠናቆ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራው ለማስጀመር ዝግጁ እንዲሆን ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች በመደበኛ፣በክረምት፣ በኤክስቴንሽን መረሃ-ግብር ሲያስተምራቸው የቆዩ 180 በመጀመሪያ ዲግሪ 2186 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 11 በፒኤችዲ ዲግሪ በድመሩ 2377 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2015ዓ.ም በዩኒቨርስቲዉ ዋና ግቢ አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ፣ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል እንዲሁም የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስተር ዲኤታ ጨምሮ የሴኔት አባላት፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዉ መግባት ጀምረዋል ።በነገው እለት ተጠቃለው እንደሚገቡም ይጠበቃል ።የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ ሐምሌ 17/2015ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/2015ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ !
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በህዳሴ አዳራሽ አካሄደ፡፡ በግምገማው ላይም የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች እና በዩኒቨርሲቲው አዲስ የተካሄደው መዋቅራዊ አደረጃጀትን ተከትሎ በአመራር መደቦች ላይ የተመደቡ አዳዲስና ነባር የካውንስል አባላት ተሳትፈዋል፡፡
We're on Social Networks. Follow us & get in touch.
Please do not hesitate to contact us:
International and Public Relations Directorate:
PoBox: 5648