2017 ዓ.ም በሀገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በ ዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ገለጻ ተሰጠ፡፡
በገለጻዉ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ፣ምክትል ፕሬዚዳንት ፣የፈተና አስተባሪዎች፣ጣቢያ ኃላፊዎች እና የፈተና ኮሚቴ ግብረ ኃይል በተገኙበት ለተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በሰላማዊና በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በፈተና ወቅት ከተፈታኝ የሚጠበቁ ግዴታዎች እና መብቶች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው በፈተና ቆይታቸው ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ህገ-ደንቦች ዙርያ ዝርዝር ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና የሚወስዱ የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ መስተዳደር እና ከኦሮምያ ክልል ከ 49 ትምህርት ቤቶች የተመደቡ ሲሆኑ በዩኒቨርስቲዉ የተቋቋመዉ ግብረ ኃይል አቀባበል እያደረገላቸዉ ይገኛል፡፡
በዩንቨርሲቲዉም ከ 7000 በላይ ታማሪዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቀ የዩንቨርስቲዉ ግብረኃይል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
የ2017 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ (ኢሲሰዩ) በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2312 ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና በፒኤች ዲ በአደዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ የመሰብሰቢየ አዳራሽ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት አስመረቀ፡፡ ከመደበኛ ፕሮግራሙ ባሻገርም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ባለው ትብብር በልዩ ፕሮግራም ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 24 ዕጩ ዲፐሎማቶችንም በከፍተና ዲፕሎማ ሰርቲፊኬት አስመርቋል፡፡
We're on Social Networks. Follow us & get in touch.
Please do not hesitate to contact us:
International and Public Relations Directorate:
PoBox: 5648