የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኝ ተከላ ስነስርአት አካሄዱ ፡፡ ስነስርአቱ የተካሄደው ዩኒቨርሲቲው በአምስት አመት ውስጥ የችግኝ ልማት ለማካሄድ ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተረከበው 3025 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ዙር በሆነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የዮንቨርስቲው ማህበረሰብ የተሳተፈ ሲሆን፣ የተተከሉት ችግኞች የውበት እና የጥላ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል የሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተተከሉት ችግኞች የማያቋርጥ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ሲገልጹ፣“ችግኝ ማሳደግ ህጻን እንደማሳደግ የማያቋርጥ እንክብካቤ ይጠይቃል፡፡” ብለዋል፡፡ አስከትለውም የተረከብነው የችግኝ መትከያ ስፍራ በከተማ መሀል የተሰጠ መሆኑን አስገንዝበው፣ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ትኩረት በመስጠት መንከባከብ እንደሚገባው አሳስበዋል፡