በሀገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ገለጻ ተሰጠ።
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ 2017ዓ.ም በሀገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ መልቀቅያ ፈተና ለመዉሰድ ለተመደቡ ተፈታኞች ሰኔ30 ቀን 2017 ዓ.ም ገለጻ ተሰጠ፡፡
በገለጻዉ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ፣ም/ፕሬዚዳንቶች ፣የጸጥታ አካላት ፣የፈተና ግብረኃይል አባላት እና ሌሎችም በተገኙበት ለተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በሰላማዊና በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፣ፈተናውን አስመልክቶ መከተል ስለሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች እና በፈተና ወቅት ከተፈታኝ የሚጠበቁ ግዴታዎች እና መብቶች ላይ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡በተጨማሪም ለበይነ መረብ ተፈታኞች ገለፃና የመግቢያ ኮድ የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በበይነ መረብ(Online Computer based) ይሰጣል፡፡
በተቋሙ የተቋቋመዉ የፈተና ግብረኃይልም የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለተፈታኝ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የመኝታ አገልግሎት ፣ የምግብ አቅርቦት እንዲሁም የህክምና አገልግሎትን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በወረቀት እና በበይነ መረብ ከሐምሌ 01/11/2017 -08/11/2017 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ያስፈትናል።