የኢሲሰዩ ለሁለት አረጋውን የቤት እድሳት ድጋፍ ለማድረግ ግንባታ አስጀመረ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ (የኢሲሰዩ) ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው የማህበረሰብ ድጋፍ እንቅስቃሴ፣ ከቆይታ ብዛት የመኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው፣ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለምዶ አልታድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለሚኖሩ ሁለት አቅመ ደካማ እናቶች ቤታቸውን አፍርሶ እንደገና ለመስራት የግንባታ ስራ አስጀመረ።
በማስጀመሪያ ኘሮግራሙ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ንጉሥ ታደሰ(ዶ/ር) እንዳሉት፣ እንደዚህ አይነቱ ሰው ተኮር የድጋፍ ስራ የመንግስት አቅጣጫ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ሰው በመሆናችን ብቻ ልናከናውነው የሚገባ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፤ አያይዘውም “በተለይ እንደእናቶቻችን ያሉ በእድሜ የገፉ ሰዎችን መደገፍ በኃይማኖቶቻችንም ቢሆን ዋጋ የሚያሰጠን ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ያሳሰቡት ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው የግንባታ ስራውን ባጠረ ጊዜ አጠናቆ ለባለቤቶቹ እንደሚያስረክብ ገልጸዋል፡፡