የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባቸውን 25 የንግድ ሱቆች በዩኒቨርሲቲው ለሚሰሩና በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 09 ለሚገኙ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በዕጣ አስተላለፈ፡፡
በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ለተጠቃሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ተጠቃሚዎቹ በተለይ አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ እንደሚሆን በመግለጽ ዩኒቨርስቲዉ እንዲህ አይነት ድጋፍ ሲያደርግ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑን በመግለጽ ወደፊትም በተቻለ መጠን ማህበራዊ ግዴታዉን እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡ የተዘጋጀው ውል በጥንቃቄ በመረዳት የተቀመጠውን ህግና ደንብ አክብረው፣ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ በአግባቡ በመወጣት ፤ በተለያዩ ነገር ግን ገበያ ተኮር ባደረጉ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን በመቻላቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም የሥራ ስኬትን ተመኝተዋል፡፡