በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 18 እስከ 21 2015 ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
ፈተናዉ በኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት በዩኒቨርሲቲው ለፈተና የተመደቡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ተገቢው አቀባበልና የሚያስፈልጓቸው ግብዐቶች በተሟላ መልኩ የቀረበላቸው ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱንና ስርዓት በተከተለ ሁኔታ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ባደረገው ኃላፊነትን በብቃት የመወጣት እንቅስቃሴ ፈተናው ያለ ምንም ችግርና እንከን የተሰጠ ሲሆን ተማሪዎቹም በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናቸው ለመውሰድ ችለዋል፡፡ በዚህ ዙር ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተደረጉት ተማሪዎች በግጭትና በተለያየ ምክንያት በመደበኛው የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ ፈተና ካልተሰጠባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡