የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠዉ የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ዝግጅቱን በማጠናቀቅ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ለዕጩ ተመራቂዎቹ ሞዴል ፈተና በዩኒቨርሲቲዉ በተለያዩ ማዕከላት ሰጠ፡፡
ዶ/ር ተመስገን ቢረጋ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት የኢሲሰዩ የመዉጫ ፈተና ዝግጅት ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል እንደነበር በመግለጽ ካለዉ ተሞክሮ በመነሳት በ2015 ለሚሰጠዉ የመዉጫ ፈተና ተማሪዎችን ሲያዘጋጅ እንደቆየ እና በ 16/10/2015 ዓ.ም ለእጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂዎች ሞዴል የመዉጫ ፈተና መስጠቱን ገልጸዋል፡፡የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚሰጥ ለዚህም ዩኒቨርሲቲዉ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እና ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በማዕከልነት እንደሚያገለግል ገልጸዋል፡፡