በአገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ገለጻ ተሰጠ።
2016 ዓ.ም በአገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ በዩኒቨርሲቲዉ ለተመደቡ ተፈታኞች ሐምሌ8 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ገለጻ ተሰጠ፡፡
በገለጻዉ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ፣ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለማ ጉዲሳ ፣የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አለማየሁ ደበበ እና የኮሌጅ ዲኖች ሌሎች የፈተና ግብረሀይል አባላት በተገኙበት ለተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በሰላማዊና በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፣ፈተናውን አስመልክቶ መከተል ስለሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች እና በፈተና ወቅት ከተፈታኝ የሚጠበቁ ግዴታዎች እና መብቶች ላይ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡ በተጨማሪም ለበይነ መረብ ተፈታኞች ገለፃና የመግቢያ ኮድ የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን ይሰጣል።በኮምፒተር (Online Computer based) በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ ሲሆን የኢሲሰዩ የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡