በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል
በ2015 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዉ መግባት ጀምረዋል ።በነገው እለት ተጠቃለው እንደሚገቡም ይጠበቃል ።የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ ሐምሌ 17/2015ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/2015ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።
ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ !