የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስልጠናና ማማከር ማዕከል የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን አስመረቀ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስልጠናና ማማከር ማዕከል ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር ለ45 ቀናት ያሰለጠናቸውን 70 ሴት ሰልጣኖች በሰኔ 15 ቀን 2014ዓ.ም በህዳሴ አዳራሽ አስመረቀ፡፡
ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ከበደ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት ‹‹ትልልቅ የስራና የቤተሰብ ኃላፊነቶችና ጫናዎችን ተቋቁማችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ ልትኮሩ ይገባቹኃል፡፡›ብላዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ በበኩላቸው ስልጠናው ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ እና በዚህ ሶስተኛው ዙር ከተለያዩ የክፍል መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሴት ሰልጣኞችን ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በተለያዩ ተፅዕኖዎች ውስጥ ሆነው የተለያዩ ሀላፊነቶችን ወስደው ለሚሰሩ ሴቶች ልዩ ትኩረትን በመስጠት የተሻለ የስራ አቅም እና ችሎታ እንዲራቸው በማስቻል ከፍተኛ ለውጥን ማምጣት ይቻላል ብለን በመሳባችን ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው የጉምሩክ አስተላላፊነትን መሰረት ያደረገና በ14 አብይ ርዕሶችን ያተኮረ ስልጠና እና ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከኢሲሰዩ በተወጣጡ አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን፤ በስልጠናው ማጠናቀቂያም ሰልጣኞቹ የመመዘኛ ፈተና ወስደዋል፡፡