የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ለመዉሰድ ለተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ገለጻ (orientation) ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በዛሬው ዕለት 25/11/2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
በማስጀመሪያው ዕለት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ እና የከፍተኛ ትምህርትና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት አጠቃላይ የፈተናውን ሂደት በተመለከተ ጉብኝት አድርገዋል።
የኢሲሰዮ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ለሚኒስትሩ አጠቃላይ ሂደቱን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉላቸዉ ሲሆን የፈተናው ሂደት ያለምንም እንከን አየተካሄደ መሆኑን ገልፀውላቸዋል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም በዮንቨርስቲው ይሰጣል፡፡