የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም እየተሰጠ ባለዉ የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመዉሰድ ለተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ገለጻ (orientation) ሐምሌ 08ቀን2016 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በዛሬው ዕለት 09/11/2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
በማስጀመሪያው ዕለት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ እና የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት አጠቃላይ የፈተናውን ሂደት በተመለከተ ጉብኝት አድርገዋል።
የኢሲሰዮ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ለሚኒስትሩ አጠቃላይ ሂደቱን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉላቸዉ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የማህበረሰብ ሳይንስ ተፈታኞች ያለምንም እንከን ፈተናቸዉን እንዳጠናቀቁ በመግለጽ የሁለተኛ ዙር የፈተና ሂደት በጥሩ ሁኔታ አየተካሄደ መሆኑን እና ለፈተናው አስፈላጊ ግብአት መሟላቱን ጠቁመው፣ በበይነ መረብ አማካኝነት ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎችም በቂ ኮምፒዩተሮች እና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳለ ገልፀውላቸዋል።በማጠቃለያም ላይ ክቡር ሚኒስትሩ አረንጓዴ አሻራቸዉን በዩኒቨርስዉ ዋና ግቢ ችግኝ በመትከል አኑረዋል፡፡
በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡