የኢሲሰዩ በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ በትምህርት ሚኒስትር በተዘጋጀዉ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች / Key Performance Indicators ስምምነት ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆነ ስምምነቱም በዋናነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ መለኪያች ላይ ያተኮረ እድገት እንዲኖራቸው፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ስራን በውጤት መምራት እንዲችሉ፣ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና ፋይዳቸው የጎላ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ላይ እንዲያተኩሩ ፣ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ እንዲፈቱ እና እንደተቋም የተጣለባቸዉን ሀላፊነት በጥራት እና በብቃት እንዲያከናዉኑ ያሚያስችል ነዉ፡፡