የኢሲሰዩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም የፊርማ ስነሥርዓት አካሄደ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀዉ በቁልፍ ተግባራት የአፈጻጸም አመላካቾች / Key Performance Indicators/ ስምምነት መስከረም 30 ቀን 2018ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆነ ስምምነቱም በዋናነት በትምህርት ዘርፉ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች መጠነ ሰፊ ለውጥ መመዝገቡን እና የዚህን ቀጣይነት ማረጋገጥ ፣በተለይ ዲጂታላይዜሽንን በማስፋፋት ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወን እንደለበት ያመላከተ ሲሆን በቀጣይም የትምህርትን ጥራት፣ ተደራሽነትና አካታችነትን በማሳደግ የትምህር ስርአት ማዘመን የሁሉም ድርሻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችም ይህን ስምምነት በልዩ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት በቁርጠኝነት ለአፈጻጸሙ ድርሻቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ተላልፏል፡፡