የኢሲሰዩ የተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ግምገማ ተካሄደ
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ 2013 የት/ዘመን የተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ከሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የሥራ ኃላፊዎች አጠቃላይ ግምገማ ጥቅምት 20/ 2013 ተደረገ፡፡
የኢሲሰዩ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ለገምጋሚ አባላቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉን ካስተላለፉ በኋላ የኢሲሰዩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመቋቋም የተቋረጠውን ትምህርትና ስልጠና ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል በዚህም ተማሪዎችን ደረጃ በደረጃ መልሶ ለመቀበል የሚያስችሉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው የስራና አፈፃፀም መመሪያ ተሰጥቶባቸዉ ለቅበላዉ የተለያዩ ዝግጅቶችም ተደርገዋል ብለዋል ፡፡
ተቋማችን የለይቶ ማቆያ በመሆን አገልግሎት ስንሰጥ መቆየታችን ብዙ ተሞክሮ እንድንወስድ አድርጎናል ለዚህም ቅድመ ዝግጅታችንን ቀድመን አከናዉነናል ማለት ይቻላል በማለት በተለይ በመጀመሪያ የኮቪድ ወቅት በሰራተኛዉ ዘንድ የነበሩ ፍራሀቶች በሙሉ አሁን እንደተቋም በግንዛቤ ስራዎች ቀንሶአል ስለዚህ ተማሪዎቻችንን ለመቀበል ብዙም አንቸገርም ፡፡ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እራሳችንን እየተከላከልን ሰላማዊ እና ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን በመፍጠር ተማሪዎቻችንን ለመቀበል ዝግጅታችንን ጨርሰናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በዝግጅት ምራፍ የተሰሩ ስራዎች ለገምጋሚዎቹ አብራርተዋል፡፡
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተወክለዉ የመጡት አባላትም በዋናነት ትምህርትና ስልጠናውን ለማስጀመር ተቋማት ያሉበትን ደረጃ በተለይ ኮቪድ 19 ከመከላከል አንጻር በተጨባጭ እየሰሩ ያሉትን ስራዎችና የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከመተግበር አንጻር መገምገም ሲሆን የዩንቨርስቲዉን አጠቃላይ የተማሪዎች ቅበላ ዝግጅት በተመለከተ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡:
በጉብኝቱም ማጠናቀቅያ ላይ ሲገልጹ የተማሪዎች መመገብያ አዳራሽ፣ቤተመጽሀፍትናዶርሚተሪዎች አጠቃላይ ኮቪድ ለመከላከል በሣይንስና ከፍተኛ ትምህርትና ጤና ሚኒስቴር የተቀመጡት ፕሮቶኮሎች እንደሚያሟሉ በተለይ ተቋሙ በተጨባጭ እየሰራቸዉ ያሉ ስራዎች ለሌላም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደ ሞዴል የሚታይ መሆኑን በሰጡት አስተያየት በመግለጽ የተቀሩትን የዝግጅት ሥራዎች በማጠናቀቅ ተማሪዎችን በታቀደው መርሀ ግብር የመቀበል ቁመና ላይ መሁኑን ገልጸዋል ፡፡በተጨማሪም ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ተማሪዎች መመሪያዎችን በጥብቅ ዲሲፒልን እንዲፈፅሙ ክትትል አስፈላጊ መሆኑን አበክረዉ አሳስበዋል፡፡