የኢሲሰዩ ፕሬዚዳንት በየዘርፉ ያሉ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ጎበኙ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ በዩኒቨርስቲዉ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል፡፡ጉብኝቱም በዋናነት ያተኮረዉ የተጀመሩ ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ፣የተጀመሩ የግንባታ ሂደቶች እና በተቋሙ ያሉ ፋሲሊቲዎች በምን ሂደት ላይ እንዳሉ የመስክ ጉብኝት ማድረግን ያካትታል ፡፡በተጨማሪም የየስራ ክፍሎች አደረጃጀት እና አጠቃላይ አሰራሮች በተመለከተ በየክፍሉ ያሉ የስራ አመራሮች ገለጻ አድርገዉላቸዋል ፡፡
ፕሬዚዳንቱም በጉብኝታቸዉ ላይ እንደተናገሩት በተቋሙ የተፈጠሩ ወደፊትም ለሚፈጠሩ አቅሞች ሙሉ በሙሉ የመጠቀም ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ በቀጣይ ለሚከናወኑ የተቋሙ ስትራቴጅካዊ ተግባራት በየዘረፎቹ ላሉ የስራ ክፍሎች ለሚሰሯቸው ማናቸውም ሥራዎች በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚጠበቁ ድጋፎች እንደሚደረጉ እና እንደ አመራርም ቁርጠኝነት መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጣቸዉን ተልዕኮዎች ለማስፈጸም እና የዩኒቨርሲቲውን ዋንኛ ግብ ዉጤታማ ለማድረግ የስልጠና ፋሲሊቲዎች አደረጃጀት እና አሰራር ማዘመን ፣በዩኒቨርሲቲው የሚገኙትን ቤተ-ሙከራዎችን ስራ ማስጀመር በተጨማሪም የICT መሠረተ ልማት አቅምን ለማሳደግ ትልቅ ስራ ከሁሉም የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል ፡፡
በጉብኝቱም በተለያዩ ዘርፍ ያሉ የስራ ክፍሎች እና ፋሲሊቲዎች ተጎብኝተዋል ፡፡