የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል
የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል
በዩኒቨርሲቲው በሁለት ዙር ለሚሰጠው ፈተና ከ8ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ሲሆን ለዚህም ተቋሙ ዝግጅቱን አጠናቋል ።
የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ እንደገለጹት ተቋሙ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ በመሆኑ ከዚህ በፊት ከፈተና አሰጣጥ ካካበተዉ ልምድ በመነሳት አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር በዩኒቨርሲቲዉ ዋናዉ ካምፓስ ከ4 ሺ በላይ ተፈታኞች ለማስተናገድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች አጠናቋል ብለዋል ፡፡ ተፈታኞች በዩኒቨርስቲዉ ቆይታቸዉ የተፈታኞች መብቶች እና ግዴታዎች በዝርዝር ገለጻ እንደሚደረግ በማሳሰብ ሁሉም ለስኬቱ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ ለተፈታኞችም ተቋሙ የመፈተኛ፣ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎቶች ዝግጁ ማድረጉን ገልጸዋል።