የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ላጋጠመው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ለማደረስ ያቋቋመዉ ቡድን በዛሬዉ እለት 03/6/2014 ዓ.ም ለመማር ማስተማር ሥራ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች በመያዝ ከዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ተነስቷል ፡፡
የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሲሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል በፌደራል ደረጃ ዩኒቨርሲቲውን ለመደገፍ ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑን በመግለጽ ድጋፉን ለማድረስ ዛሬ ከዩኒቨርሲቲዉ ዋና ካምፓስ አንድ ቡድን የተነሳ መሆኑን ይህም ድጋፍ ወደፊት የዩኒቨርሲቲዉ አቅም በፈቀደ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ፋሲካ ደረጀ እንደገለጹት ድጋፉ በዋናነት ተቋሙ ትምህርት እንዲያስጀምር እገዛ የሚያደርጉ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል የተለያዩ የቢሮና የተማሪ ወንበሮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒተር ፣ዴስክቶፕ ኮምፒተር፣ ፕሮጀክተር፣ፕሪንተር፣የተለያዩ ወንበሮች፣ለተማሪ የምግብ አገልግሎት የሚውሉ የካፍቴሪያ ዕቃዎች ፣ፍራሾች፣ የመጽሀፍ መደርደሪያዎች እና ሌሎችም አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች መካተታቸዉን ገልጸዋል፡፡