የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑ ተገለጸ
በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የምርምር አገልግሎቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የምርምር ማዕከል ጨምሮ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን ተመልክቷል፡፡
የደሞዝ ማነስ፣ የትምህርት እና ጥቅማጥቅም አከፋፈል ወጥ አለመሆን፣ የውድድር ሂደቶች ሚዛናዊ አለመሆን፣ የጥናትና ምርምር በጀቶች ወደስራው ባለቤት አለመድረስ፣ የተማሪዎች የምግብ በጀት እጥረትና መኝታ ክፍል መጣበብ የሚሉት ከዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ጋር በነበረው ውይይት የተነሱ ነጥቦች ናቸው፡፡
የአሰራር ክፍተቶችንና የምርምር ውጤቶችን ኩረጃ ለመቀነስ ግልጽ የሆነ መመሪያ ማውጣት እንዳለበት እንዲሁም ከኑሮ ውድነት አንጻር የሀገራችን ኢኮኖሚ እስኪረጋጋ መንግስት የታክስ ስረዛ ቢያደረግ የሚሉት አስተያየቶች እና ሀሳቦችም ተነስተዋል፡፡
የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ ታደሰ በዛ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ተመራጭ ለመሆን በመቀናጀት፣ አሳታፊ እና ግልጽ በሆነ አሰራር አገልግሎት መስጠት እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሪፎርም ምሳሌዎችን በማመንጨት ለውጥ ያሳየ ተቋም እንደሆነና ዝቅተኛ ተከፋይ ሰራተኞችን ለመደገፍ የተሰራው ስራ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ አደረጃጀት ለምርምር አመቺ እንዲሆን ከግንባታ ጀምሮ መስራት እንደሚያስፈልግ እና የምርምር ተነሳሽነትን ለማምጣት አሰራሮችን ግልጽ በማድረግ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ እና ሌሎች አመራሮች ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ አስተያየቶችን ለቀጣይ እንደ ግብአት በመውሰድ እንደሚሰሩና የታየው ውጤትም የሁሉም ሰራተኛ አስተዋጽኦ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
(ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 29፣ 2015 ዓ.ም፤ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የምርምር አገልግሎቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የምርምር ማዕከል ጨምሮ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን ተመልክቷል፡፡
የደሞዝ ማነስ፣ የትምህርት እና ጥቅማጥቅም አከፋፈል ወጥ አለመሆን፣ የውድድር ሂደቶች ሚዛናዊ አለመሆን፣ የጥናትና ምርምር በጀቶች ወደስራው ባለቤት አለመድረስ፣ የተማሪዎች የምግብ በጀት እጥረትና መኝታ ክፍል መጣበብ የሚሉት ከዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ጋር በነበረው ውይይት የተነሱ ነጥቦች ናቸው፡፡
የአሰራር ክፍተቶችንና የምርምር ውጤቶችን ኩረጃ ለመቀነስ ግልጽ የሆነ መመሪያ ማውጣት እንዳለበት እንዲሁም ከኑሮ ውድነት አንጻር የሀገራችን ኢኮኖሚ እስኪረጋጋ መንግስት የታክስ ስረዛ ቢያደረግ የሚሉት አስተያየቶች እና ሀሳቦችም ተነስተዋል፡፡
የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ ታደሰ በዛ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ተመራጭ ለመሆን በመቀናጀት፣ አሳታፊ እና ግልጽ በሆነ አሰራር አገልግሎት መስጠት እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሪፎርም ምሳሌዎችን በማመንጨት ለውጥ ያሳየ ተቋም እንደሆነና ዝቅተኛ ተከፋይ ሰራተኞችን ለመደገፍ የተሰራው ስራ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ አደረጃጀት ለምርምር አመቺ እንዲሆን ከግንባታ ጀምሮ መስራት እንደሚያስፈልግ እና የምርምር ተነሳሽነትን ለማምጣት አሰራሮችን ግልጽ በማድረግ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ እና ሌሎች አመራሮች ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ አስተያየቶችን ለቀጣይ እንደ ግብአት በመውሰድ እንደሚሰሩና የታየው ውጤትም የሁሉም ሰራተኛ አስተዋጽኦ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ምንጭ House of Peoples Representatives of FDRE የፊስቡክ ገጽ