የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማጠቃለያ ፈተና (Entrance Exam)የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ።
ኢሲሰዩ በ2016 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና(Entrance Exam)የሚወስዱ በዩኒቨርሲቲዉ የተመደቡ ተማሪዎች ተቀብሎ ለፈተናዉ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እያስተናገደ ይገኛል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣዉ መረሃ ግብር መሰረት ፈተናዉ የሚሰጠዉ በሁለቱም የትምህርት ዘርፍ ማለትም በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበረዊ ሳይንስ ሲሆን፤ በቅድሚያ ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚሰጥ ሆኖ በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ፡፡ በመጀመሪያዉ ዙር በዩኒቨርስቲዉ ለፈተና የሚቀመጡ የማህበረዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ 4000 ሺ የሚጠጉ ተፈታኞች ናቸዉ ።
ለተፈታኞች ከዩኒቨርስቲዉ የተዋቀረዉ የፈተና ግበረሀይል ኮሚቴ አቀባበል እያደረጉላቸዉ ይገኛል፡፡