15 ኛዉ የኢትዮጲያ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በኢሲሰዩ ተከበረ
የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 15ኛዉን የብሔር ብሄረሰቦችናሕዝቦች ቀን “እኩልነትና ሕብረ-ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቀል ከ23/3/2013-24/3/2013 ዓ.ም በአባይ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ፡፡
በመክፈቻ ንግግራቸዉ ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር የተዋቀረችዉ በብሄር ብሔረሰቦችናህዝቦች ስብስብ ነዉ ፡፡ በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መንግስታት ተለዋዉጠዋል፤ የተለያዩ ችግሮችም አልፈናል ነገር ግን ኢትዮጲያ አንድነቷንናሉአላዊነቷን ጠብቃ ቆየታለች ወደፊትም ትቀጥላለች፡፡ብዝኃነታችንን ደግሞ ለሰላም፣ለልማትና ለሁለንተናዊ ብልፅግና ይበልጥ መጠቀም ይገባናል ብለዋል፡፡እኛ ኢትዮጵያዉያን የቆየውን የአብሮነትና የአንድነት እሴቶች ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን የለዉጥ ጉዞ ወደ ፊት ማራመድ ከሁሉም ሀገር ወዳድ የሚጠበቅ ነዉ ብለዋል፡፡
የፖለቲካ አስተሳሰብና ልዩነት በጠረፔዛ ዙርያ አለመፍታት ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል ስለዚህም እኛ ምሁራን የመፍቴህ ሀሳብ አመንጪ መሆን አለብን ፡፡ እንደ ተቋም ስንሰራ በየኔነት ስሜት እየሰራን እራሳችንንና ሀገራችንን እንድንጠቅም ልዩነታችንን እንደውበት ለተሻለ አንድነታችን እናዉለዉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ሰራተኛዉም በሀገራዊ ጉዳዮች የነቃ ተስትፎ እንዲያደርግ በዚህ መድረክም ሀሳቡን በግልጽነት ካለምንም የሀሳብ ቁጠብነት እንዲገልጽ በማሳሰብ የእለቱን ፕሮግራም አስጀምረዋል፡፡
በእለቱ ለዉይይት መነሻ የሚሆኑ ሁለት ጽሁፎች ማለትም አገራዊ ሪፎርም ለጠንካራ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት ግንባታ(ነጻ፣ገለልተኛናብቃት ያላቸዉ ተቋማት ግንባታ እንደወሳኝ የሪፎርም አጀንደ) እና በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ በዶ/ር አለማየሁ ደበበ የምርምርና ማህበረሰብ ም/ፕሬዚዳንት እና በዶ/ር ዋቃሪ ነጋሪ የስልጠናናማማከር ም/ፕሬዚዳንት ቀርቦአል፡፡ በተጨማሪም በተጠቀሱት ርእሰ ጉዳዮች ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ የዩንቨርሲቲዉ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ አወያይነት ከዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዉይይት ተካሄዶአል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በተነሱት ሁለት አበይት ርዕሶች ላይ የተወያዩ ሲሆን በዚህም የተለያዩ ሀሳቦች፣ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተንሸራሽረዋል፡፡ በቀጣይም እንደነዚህ አይነት በዓላት በይበልጥ እየተጠናከሩ ቢቀጥሉ የመወያያ መድረኮች ቢዘጋጁናእኛም ሃሳባችንን ብንገልጽ ልዩነቶችን እያጠበብን የምንሄድበትና ችግሮችም ሳይባባሱ በጊዜ መፍትሄ የምናፈላልግበት መድረክ ስለሚሆን ወሳኝ ሚና መጫወት እንችላለን በማለት አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡