የኢ.ሲ.ሰ.ዩ ለ2015 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ለሚመረቁ ተማሪዎች የምረቃ ፅሑፍ አዘገጃጀት ሥነ ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ህዳር 14-2015 አ.ም በአባይ አዳራሽ ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የተዘጋጀው በስርዓተ-ፆታ እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ሲሆን፤ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ በ2015 ለሚመረቁ ሴት፣ አካል ጉዳተኛና ከአርብቶ አደር አካባቢ ለመጡ ተማሪዎች በጥናትና ምርምር ፅሑፍ አቀራረብ ዙሪያ መከተል ያለባቸውን መንገዶች ምን መምሰል እንዳለበትና ሊከተሏቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ማስገንዘብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስልጠናው በተለያዩ መንገዶች በቴሌግራም በኢሜልና በአካል በየአመቱ ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑ ስልጠና ለ123 ተማሪዎች በተጠቀሰው ርእሰ ጉዳይ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ በቀጣይም ከዚህ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ዝናቤ ታደሰ የስርዓተ-ፆታ እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡