የኢሲሰዩ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና የሚወስዱ የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ መስተዳደር እና ከኦሮምያ ክልል ከ 49 ትምህርት ቤቶች የተመደቡ ሲሆኑ በዩኒቨርስቲዉ የተቋቋመዉ ግብረ ኃይል አቀባበል እያደረገላቸዉ ይገኛል፡፡
በዩንቨርሲቲዉም ከ 7000 በላይ ታማሪዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቀ የዩንቨርስቲዉ ግብረኃይል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
የ2017 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡