የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ገለጻ ተሰጠ።
2017 ዓ.ም በሀገርአቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በ ዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ገለጻ ተሰጠ፡፡
በገለጻዉ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ፣ምክትል ፕሬዚዳንት ፣የፈተና አስተባሪዎች፣ጣቢያ ኃላፊዎች እና የፈተና ኮሚቴ ግብረ ኃይል በተገኙበት ለተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በሰላማዊና በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በፈተና ወቅት ከተፈታኝ የሚጠበቁ ግዴታዎች እና መብቶች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው በፈተና ቆይታቸው ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ህገ-ደንቦች ዙርያ ዝርዝር ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡
የአንደኛ ዙር ተፈታኞች ከሰኔ 23ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን ፈተናዉ ለሚቀጥሉት 3 ተከታታይ ቀናትየሚከናወን ይሆናል። ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኝ መምህራን እና ጣቢያ ኃላፊዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ቀደም ብለዉ በመምጣት ለፈተናው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ከዩኒቨርስቲዉ ዋና ግብረኃይል ጋር በመቀናጀት አጠናቀዋል፡፡