የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ ፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 23/10/2017- 25/10/2017 ዓ.ም ድረስ በበይነ መረብ እና በወረቅት ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን ሙሉ በሙሉ ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል ።
የኢሲሰዩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ በሰላም የተጠናቀቀ መሆኑን በመጥቀስ ፈተናዉ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅረበዋል፡፡ ይህን ኃላፊነታችዉንም በተቀናጀ መልኩ በቀጣይ ጊዜ ለሚሰጠዉ የማህበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ፍፁም ሰላማዊና ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የየራሳቸዉን ድርሻ እና ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡