የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዙር የተቀበላቸውን የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በማስፈተን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ።
ከሐምሌ 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የተፈጥሮ ሣይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ፈተና በዛሬው ዕለት ሐምሌ 28/2015 ዓ/ም ሠላማዊ እና በተረጋጋ መልኩ ተጠናቋል፡፡ ተማሪዎችም ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
ከሀገሪቱ ከተለያዩ ቦታ የመጡ የፈተና አስፈፃሚዎች በግቢ በነበራቸው ኃላፊነት ግቢ ከገቡበት ቀን ጀምሮ ፈተናው እስከተጠናቀቀበት ድረስ በነበራቸው ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩ ከጎናቸው በመሆን ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ተፈታኞችም ፍፁም በተረጋጋ እና በሰላማዊ ሁኔታ ፈተናውን የወሰዱ መሆናቸዉን ገልጸዋል።